የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ፕሬዝደንት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ህብረቱ በግብጽ ላይ የጣለው የአባልነት እቀባ፤ ካይሮ ወደ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት ስትመለስ እንደሚስተካከል ተናገሩ።
አቶ ኃይለማርያም ይህንን የአፍሪካ ህብረት አቋም አዲስ የተመሰረተው የግብጽ ጊዚያዊ መንግስት ልዑካንን በጽህፈት ቤታቸው አግኝተው ካነጋገሩ በኋላ ነው።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ማምሻውን ለቪኦኤ እንዳስታወቁት፤ የአፍሪካ ህብረት ለግብጽም ሆነ ተመሳሳይ ወታደራዊ መፈንቅለ-መንግስት ለተካሄደባቸው እንደ ማሊ፣ ማዳጋስካርና ሌሎች የአፍሪካ አገሮች ያለው መስፈርት ተመሳሳይ ነው ብለዋል።
ግብጽ የአፍሪካ ህበረት የጣለባትን የአባልነት እቀባ እንዲያነሳ የጠየቀች ሲሆን፤ የአፍሪካ ህብረት አቋሙ የሚቀየረው በህዝብ የተመረጠ መንግስት ሲኖር እንደሆነ ገልጿል።
ግብጻዊያን ልዑንም በአዲስ አበባ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ጋር ሁለቱ አግሮች በአባይ ወንዝ የውሃ አጠቃቀም ዙሪያ የጀመሩትን ውይይትና ትብብር እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያም ትብብሩ እንደሚቀጥል አረጋግጣ፤ የካይሮ የጸጥታ ሁኔታ ሲሻሻል፤ ከማህበረሰቡና ከመንግስት የተውጣጣ የልዑካን ቡድን ወደ ግብጽ እንደምትልክ ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።