የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትን የሚያጋጥሙ ከአየር ንብረት ጋራ የተያያዙ አደጋዎች ከጊዜ ወደጊዜ እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ በመኾኑም የቀጣናውን ሀገራት ያሰባሰበው ኢጋድ ሀገራቱ ከሰብአዊ ረድዔት ተቋማት ጋራ በመኾን የአደጋ ዝግጁነት መርሐ ግብሮችን በማሰናዳት ላይ ይገኛል፡፡ ዓላማውም በስምንቱም የቀጣናው ሀገራት የአደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዐቶች በመዘርጋት አደጋዎች ቢከሰቱ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመቀነስ እንዲቻል መኾኑን ከናይሮቢ በጁማ ማጃንጋ ያደረሰን ዘገባ አውስቷል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም