ጽሁፉ ለኢትዮጵያ የጂቡቲ ወደብ አስፋላጊነት ቀጣይ የሚሆነው እየተጠናከረ በመሄድ ላይ ባለው ኢኮኖሚዋ ምክንያት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ በነበረው ከባድ ድርቅ ምክንያት በምግብ ረድኤት የተሞሉት መርከቦች ጭነታቸውን ማራገፍ ስለሚኖርባቸው ነው ይላል ።
ካለፈው ሃሙስ ወዲህ እንኳን 16 መርከቦች 609,000 ሜትሪክ ቶን የሚሆን የስንዴ፣ የገብስና የዘንጋዳ ጭነት ለማራገፍ እየጠበቁ ነው። 128,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴ፣ ዘንጋዳና ማዳበርያ የጫኑ አራት መርከቦች ደግሞ ጭነታቸውን እያራገፉ መሆናቸውን ዘገባው አክሏል።
በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች መሀር ከ50 እስከ 90 ከመቶ በመሰናከሉ ከሰሀራ በታች ካሉት የአፍሪቃ ሃገሮች ትልቅዋ ስንዴ ተጠቃሚ የሆነችው ኢትዮጵያ የደረሰባትን የምግብ እጥረት ለማቃለል ስትል የስንዴ ግዢዋን ከፍ ለማድረግ ተገዳለች ካለ በኋላ ጽሁፉ የወደቡ ባለስልጣኖች ቀድሞ መያዝ ያለበት የትኛው መሆኑን መወሰን እንዳስቸገራቸው የጅቡቲ ወደቦችና የነጻ ቀጣና ሊቀመንበር እንዲሁም ዋና ስራ አስፈጻሚ አቡበከር ዑመር መናጋራቸውን ጠቁሟል።
ቢቢሲ (BBC) ማለት የብሪታንያ የዜና ስርጭት ኮርፐረሽን በበኩሉ ብሪታንይ ከአውሮፓ ህብረት አባልነት እንድትወጣ ድምጽ ስለሰጡ አፍሪቃውያን መጤዎች ዘግቧል። አፍሪቃውያን ለንደን ውስጥ የሚኖሩት ዊልያም ሼክስፒር ስለ ኦቴሎ ታሪክ ከመጻፉ በፊት ቀደም ብለው ነው። ከዚያ በኋላ ደግሞ የብሪታንያ ኢምፓየር ማለት ንጉሳዊ አገዛዝ እየሰፋ በሄደበት ጊዜና መስፋፋቱ ባበቃበት ወቅትም ብዙ አፍሪቃውያን ለንደን ከተማን መኖርያቸው ሲያደርጉ ቆይተዋል። ለከተማይቱ ህብረ-ባህላዊ ገጽታንም አስተዋጽኦ አድርገዋል ይላል የቢቢሲው ዘገባ።
ከአምስት አመታት በፊት በወጣው የህዝብ ብዛት ቆጠራ መሰረት ከኢንግላንድና ከዌልስ ህዝብ 1.8 ከመቶ የሚሆኑት ጥቁር አፍሪቃውያን ነን ይላሉ። ከሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች ጋር ሲነጻጸር አፍሪቃውያን በብሪታንያ ለሚያገኙት እድልና የሀገርቱ ህግ ለሚሰጣቸውን ዋስትና ዋጋ ይሰጣሉ።
ሌላው ሲነሳ የቆየው ነጥብ ደግሞ ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት አባልነት እንድትወጣ የመረጡት አፍሪቃውያን እንደሌሎቹ የአገሬው ተወላጅ እንግሊዛውያን ሁሉ የአዲስ ፋላሾች መግባት እንደሚያሳስባቸው ዘገባው ሲያብራራ የስራና የቤት ገባያዎች ይጣበባሉ የሚል ስጋት እንዳለባቸው ገልጿል።
አንዳንድ ሶማሊዎች ግን በሌሎች የአውሮፓ ሃገሮች ካሉት የሶማልያ ተወላጆች ጋር ባላቸው ግንኙነት ምክንያት ብሪታንያ በአውሮፓ ህብረት አባልነት እንድትቀጠል መምረጣቸውን ቢቢሲ ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ዘገባ ጠቁሟል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፍይል ያድምጡ።