በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲስ ቴክኖሎጂ በአፍሪካ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ለውጥ ለማምጣት


ሃለኩ መልካ ጢሴ የእርሻ ልማት፡-በኢትዮጵያ የሞባይል ስልክ በገጠርም ተስፋፍቷል
ሃለኩ መልካ ጢሴ የእርሻ ልማት፡-በኢትዮጵያ የሞባይል ስልክ በገጠርም ተስፋፍቷል

በአለም ዙሪያ በጨቋኝ አገዛዞች ስር የሚኖሩ ዜጎች በድረ-ገጽ፣ በሞባይል ስልኮችና በተለያዩ አዳዲስ ቴክኖሎጂ በመገልገል በማህበረሰባቸው ለውጥ ለማምጣት እንዲችሉ የሚያገዙ መዋቅሮች ዜጎች ድምጻቸውን እንዲያሰሙና መብቶቻቸውን እንዲያስከብሩ አስችለዋል።

በቅርቡ በሰሜን አፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ በተለምዶ የሚታወቁት የብዙሃን መገናኛ እንደ ሬድዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ጋዜጦችና ሌሎች ህትመቶችን በስፋት ያልተጠቀመ በማህበራዊ ድረ-ገጾችና የቴክስት መልእክቶችን በመጠቀም፤ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች ሲደራጁ ታይቷል።

በኒች የአለም አቀፍ ጥናቶች ተቋም የተሰናዳው ውይይት፤ በተለምዶ በዋሽንግተን በአፍሪካ ጉዳዮች እንደሚታዩ ውይይቶች ለዘመናት ልምድ ያካበቱ ተናጋሪዎች ያሉበት አልነበረም።

አብዛኖቹ ወጣቶች ናቸው። አሳቡም በአፍሪካ ሊሰሩ የሚችሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ የመገናኛ መንገዶችና በተግባር የታዩ ተሞክሮዎች ላይ ማተኮር ነው።

ኢንቪኒዮ የሚባለው ድርጅት የሚሰራው የመገናኛ ቴክኖሎጂን በጣም ለሚፈልጉ ሰዎች መረጃ ማድረስ ነው ።

ፍሮንት ላይን ኤስ. ኤም. ኤስ. የሚባለው ድርጅት ደግሞ የሚሰራው በሞባይል ስልክ የቴክስት መልእክቶችን ማስተላለፍ ነው። ሰዎች በእጃቸው የሚገኘውን ስልካቸውን ተጠቅመው መረጃ እንዲያገኙ ማስቻል።

በአፍሪካ ከመረጃ ርቀው የሚኖሩ ሰዎች በአካባቢያቸው ከሉ ነባር የመረጃ አውታሮች ውጭ ተጨማሪ መረጃ እንዲያገኙ፣ ሀሳባቸውንና ችግሮቻቸውን፤ እንዲሁም የመፍትሄ አሳቦቻቸውን የሚገልጹበት መድረክ መፍጠር ነው አላማው።

ግቡ የተመጠነ፣ የተቀላጠፈና፣ በማንኛውም ጊዜ ዜጎች በአካባቢያቸው፣ እንዲሁም በቀጥታ የነርሱን ኑሮ የሚነካና በተዘዋዋሪ የሚመለከቷቸውን ጉዳዮች አስመልክቶ መረጃ እንዲያገኙ ነው። ይሄንን መረጃ ተጠቅመው ህይወታቸውን የሚመሩበትን እራሳቸው የመረጡትን መንገድ ማፈላለግ ይሆናል።

ዌን ቮዳ ኢንቬኒዮ የተባለ፤ በቀላል ወጭና ብዙ የኤሌትሪክ ሃይል ሳይጠቀሙ የድረ-ገጽ ወይም ኢንተርኔት አገልግሎትን ወደ አፍሪካ መንደሮች ለማዳረስ የሚሰራ በአሜሪካ መሰረቱን ያደረገ ድርጅት ውስጥ ነው የሚሰራው።

ኢንቪኒዮ ከና ከጅምሩ በርካታ ችግሮች ገጠሙት። አንደኛ በገጠር አካባቢ መብራት የለም። ሲቀጥል ብዙ አበሳዎች አሉበት፤ የኢንተርኔት ግንኙነቱ በጣም ያዘገመ ነው፣ በጣም ውድ ነው፣ ሰዎች ኮምፒውተር መገልገል አይችሉም፣ በአግባቡ የሰለጠኑ የኮምፒውተር ጠጋኞች የሚገኙት በትላልቅ ከተማዎች ነው።

“ይሄንን ችግር ለመቅረፍ በገጠር አካባቢዎች በመስኩ የሚሰሩ የቴክኖሎጂ ግኝቶችን እናፈላልጋለን። ከዚይ በገጠር የሚኖሩ ሰዎች የሚፈልጉትንና በቀላሉ ሊገለገሉበት የሚችሉትን እንመርጣለን” ይላል ቮዳ።

“አንዳንድ ጊዜ ሰዎች የሚለግሱን እቃዎች አፍሪካ ውስጥ አይሰሩም። ምን አደረግን…በአካባቢው የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ ሱቆችን ያዝን። እነዚህ ሰዎች ንግድ ጀምረዋል፤ የራሳቸው ስራ ስላላቸው እዚያው ቆይተው ትርፍ ለማግኘት ይሰራሉ።”

በቀኝ ዌን ቮዳ እና ሾን ማክዶናልድ የፈጠራ ስራዎቻቸውን ሲያስረዱ
በቀኝ ዌን ቮዳ እና ሾን ማክዶናልድ የፈጠራ ስራዎቻቸውን ሲያስረዱ

ለነዚህ የኢንተርኔት ካፌዎች ጥቂት የኤሌትሪክ ሀይል የሚጠቀሙ ኮምፒውተሮችን ማቅረብና፤ የተቀላጠፈ አገልግሎቶችን ሊያገኙ የሚችሉባቸውን የቴክኖሎጂ አማራጮች ኢንቬንዮ ማፈላለግ ጀመረ። ከጸሃይ ሀይል ኤሌትሪክ የሚያመነጭ ቴክኖሎጂ ከዋጋ ውድነቱ አንጻር የሚታስብ አልነበረም፤ ሀይል ቆጣቢ ኮምፒውተሮች ግን በገበያ ላይ ይገኛሉ። እነዚህን ለማቅረብ ተቻለ።

ኢንቪንዮ አሁን በተለያዩ የአገሮች ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች መረጃ እንዲያገኙ ማስቻሉን ይናገራል።

ሌላኛው የውይይቱ ተሳታፊ ሾን ማክዶናልድ ነው። ፍሮንት ላይን SMS የሚባል ድርጅት ውስጥ ይሰራል። ይሄ ድርጅት በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ሰዎች መሰረታዊ የሞባይል ስልክ ተጠቅመው ለዘመዶቻቸው ገንዝብ የሚልኩበት፣ የባንክ ሂሳባቸውን የሚመለከቱበት፣ የገበያ ዋጋን የሚጠያየቁበት መንገድን ፈጥሯል።

“በአለማችን አምስት ቢሊዮን የሚሰሩ የሞባይል ስልኮች አሉ። ይሄ ቀላል አይደለም። አለማችን ካሏት የመገናኛ ዘዴዎች በእጂጉ የበዛና የተቀላጠፈ መረጃ ማስተላለፊያ መንገድ ነው” ብሏል።

የሞባይል ቴክስት የመረጃ አገልግሎት በጣም ርካሽና ለመገልገልም ቀላል ነው። አንድ ብዙም ያልተካበደ መሰረታዊ የሞባይል ስልክን ከኢንተርኔት በዪ-ሴስ ቤ ኬብል አገናኝቶ የፍሮንት ላይን SMS ሶፍትዌርን ወደ ስልኩ ማስተላለፍ፤ ከዚያ ስልኩ በተፈለገበት ቦታ ሁሉ ለብዙ ሰዎች መረጃ ማስተላለፍ የሚችል ይሆናል ማለት ነው።

ይሄ ሶፍትዌር ወይንም የኮምፒውተር ቋንቋ ለግብረ ሰናይ ድርጅቶችና ለማህበረሰብ ተቋማት በነጻ ሊገኝ ይችላል።

የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት እንደዚህ መሰል ቴክኖሎጂዎች በአለም ዙሪያ እንዲስፋፉ ይፈልጋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን በአለም ዙሪያ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅሞ የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ግቦች ለማሳካት የሚቻልበትን መንገድ የሚያፈላልግ “የ21ኛው ክፍለዘመን አዲስግኝት” የሚባል ዘመቻ ከፍተዋል።

ኬቲ ዳውድ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የዚህ ዘመቻ ሰራተኛ ናት። በምስራቅ አፍሪካ ከአንድ አመት በፊት የአዲስ ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች በአፍሪካ የሚሰራ ድንቅ ፈጠራቸውን አይቶ ሽልማት የሚሰጥ ውድድር አዘጋጅቶ ነበር።

የመጀመሪያው “I-COW” የሚባል ሶፍትዌር ነው። ምንድን ነው የሚያደርገው ከብት አርቢው የላሙን ድምጽ በስልኩ ይቀዳና ለመውለድ የቀሯትን ቀናት ይነግረዋል።

ዳኞቹ ይሄንን አሳብ በጣም ነው የወደዱት። ከብት አርቢዎች ላማቸው መቼ እንደምትወልድ ለማወቅ ስለሚፈልጉ

ሁለተኛው ደግሞ ስሙ “kleptocracy fighters” ይባላል። ጉቦንና ሙስናን ለመዋጋት የሚፈልጉ መንግስታት ከዜጎቻቸው መረጃ እንዲያገኙ ያስችላል። ይሄ መረጃ በድምጽና በቴክስት የሚተላለፍ ነው፤ ሰዎቹም ማንነታቸው አይታወቅም።

ሌሎችም ፈጠራዎች ለውድድሩ ቀርበዋል። ታካሚዎች ወይም እርጉዝ እናቶች ለሆስፒታል የሚሆን ገንዘብ እንዲያስቀምጡ የሚረዳ ፈጠራም ነበረበት።

ይሄ ሁሉ በቀጥታ አፍሪካ ላሉባት ችግሮች መፍትሄ ይሆናል ባይባልም። ችግሮችን የመፍቻ መንገዶችን ከተለመደው ወደ መንግስት ከማንጋጠጥ፣ ፈቃድና ይሁንታን ከመጠበቅና በተለይ ደግሞ አማራጭን ከማግኘት አንጻር፤ ለውጥ ያመጣል የሚል እምነት ተጥሎበታል።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG