የአፍሪካ ኅብረት በተያዘው የአውሮፓውያን ዓመት ለነፃ ንግድ ቀጣና መተግበር ትኩረት እንደሚሰጥ በአዲሱ ሊቀመንበሩ በኩል አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ሲካሔድ የቆየው የኅብረቱ መደበኛ ጉባዔ ሲጠናቀቅ፣ አዲሱ ሊቀመንበር አዛሊ አሱማኒ በአፍሪካ የነፃ ንግድ እንዲቀላጠፍ በትኩረት እንደሚሠራበት ተናግረዋል።
የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ባለሞያ ደግሞ “የነፃ ንግድ ትግበራው ቀላል አይሆንም” ብለዋል፡፡
የአፍሪካ ንግድ ምክርቤቶች ዋና አስተዳዳሪ አቶ ክቡር ገና ሲናገሩ፣ “በየሀገራቱ ያለው የመገበያያ ገንዘብ ልዩነት፣ የጉምሩክ አሠራር፣ የሎጂስቲክስና የመሰረተ ልማት ችግሮች በአህጉሩ የነፃ ንግድ ቀጣናን ለመተግበር ፈታኝ ያደርጉታል” ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነቱ የበለጠ ተጠቃሚ የሚሆኑት ትልቅ ኢኮኖሚ ያላቸው ሀገሮች ስለሆኑ፣ አካሔዱ ጥንቃቄ የሚፈልግ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።