በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምሥራቅ አፍሪካ አገሮችን ለመርዳት የተመከረበት የዳያስፖራ ጉባኤ


የምሥራቅ አፍሪካ አገሮችን ለመርዳት የተመከረበት የዳያስፖራ ጉባኤ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:28 0:00

ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በስደት ለመጡ ብዙዎች፣ እትብታቸው የተቀበሩባቸውን የትውልድ አገሮቻቸውን አስበው መርዳት፣ በሕይወታቸው ትልቅ ሥፍራ ከሚሰጧቸው ቁም ነገሮች አንዱ ነው።

በቅርቡ፣ መገኛቸው ከምሥራቅ አፍሪካ አገሮች የሆኑ የዳያስጶራ አባላት የተሰባሰቡበት አንድ ቡድን፣ በትውልድ አገሮቻቸው ያሉ ወገኖቻቸውን ለማገዝ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይቷል።

ውይይቱ የተካሔደው፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በአዘጋጀውና ለሁለት ቀናት በዘለቀው መርሐ ግብር ላይ ሲኾን፤ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች እና የዳያስፖራ ማኅበረሰብ መሪዎች፥ ለተወለዱባቸው አገሮቻቸው የምጣኔ ሀብት ዕድገት፣ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት በሚያስችሏቸው መንገዶች ላይ መክረዋል፡፡

የዘገባውን ዝርዝር ከተያያዘው ማጫወቻ ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG