የአፍሪካ ሀገሮች የግብርና ሚንስትሮች በዚህ ሳምንት ዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ላይ ጉባኤ ላይ ናቸው። የተሰበሰቡት የአህጉሪቱን የምግብ አመራረት ሥርዐቶች ለማሻሻል ስለሚቻልበት መንገድ ለመምከር ነው። ሚንስትሮቹ አፍሪካ ከውጭ በሚገባ ምግብ ላይ መተማመኗን ለመቀነስ ብሎም የአሕጉሪቱን አስተራረስ ከአየር ንብረት ለውጡ እና ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋራ በሚጣጣም መንገድ ለማሻሻል በታለመው የዐስር ዓመት ዕቅድ ከስምምነት ለመድረስ ተስፋ ማድረጋቸውን ጠቅሶ መሐመድ ዩሱፍ ከናይሮቢ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም