በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍጋን እስላማዊ መንግሥት የሺአ ሙስሊሞችን ኢላማ ላደረጉት ጥቃቶች ኃላፊነቱን ወሰደ


የቦምብ ፍንዳታ የደረሰበት መስጊድ ሻሪፍ ግዛት፣ አፍጋኒስታን፣ ሚያዚያ 21/2022
የቦምብ ፍንዳታ የደረሰበት መስጊድ ሻሪፍ ግዛት፣ አፍጋኒስታን፣ ሚያዚያ 21/2022

በአፍጋኒስታን ከእስላማዊ መንግሥት ጋር ግንኙነት ያላቸው የአፍጋን እስላማዊ ቡድኖች፣ አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን የሺአ ሙስሊሞችን ኢላማ ላደረገው የትናንቱ የቦምብ ጥቃት ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ አስታውቀዋል፡፡

ትናንት ሀሙስ በሰሜን አፍጋኒስታን ማዛሬ ሸሪፍ ውስጥ በሚገኘው የሺአ እምነት ተከታይ ሙስሊሞች መስጊድ ላይ በደረሰው የቦምብ ጥቃት 12 ሰዎች መሞታቸውና ወደ 40 የሚደርሱ ሰዎች መቁሰላቸውን የሆስፒታል ባለሥልጣናት ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ጥቃት ካቡል ውስጥ ደሸ ኢባርኪ በተባለ የሺአመንደር ከሚገኝ፣ የወንዶች ትምህርቤት አቅራቢያ፣ ከመንገድላይ የተጠመደ ቦምብ ሁለት ህጻናት ወንዶችን ማቁሰሉ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG