ዋሺንግተን ዲሲ —
ከአውቶቡስ ተሳፋሪዎች መካከል የሚበዙት ሴቶች እና ህፃናት እንደነበሩ አንድ የክፍለ ሀገሩ ባለሥልጣን አስታውቀዋል፡፡ ለጥቃቱ ኃላፊ ነኝ ያለ እስካሁን ባይኖርም በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የታሊባን ታጣቂዎች አዘውትረው የመንግሥት ባለሥልጣናትን እና የፀጥታ ኃይሎችን ዒላማ ያደረጉ ቦምቦችን መንገድ ዳር ይቀብራሉ።
ጥቃቶቹ እየተፈፀሙ ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ባለልስጣናት እና የታሊባን ተወካዮች ያሳተፈው የሰላም ድርድር ሊቀጠል በታቀደበት በአሁኑ ወቅት ነው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ