በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአፋር የተፈናቀሉ ሰዎች ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ነዋሪዎች ገለፁ


የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማ ሰመራ
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማ ሰመራ

የህወሓት ኃይሎች በአፋር ኪልበቲ ረሱ ዞን አዲስ ከፍተውታል በተባለው ጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉና ወደ ሠላማዊ መጠለያ ያልደረሱ ወደ 150 ሺሕ የሚደርሱ ተፈናቃዮች የት እንደሚገኙ አለመታወቁን ነዋሪዎች ገለፁ።

የአፋር ክልል መንግሥት ከሦስት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ የኢትዮ ጂቡቲ የባቡር መሥመር መአከል የሆነችውን የሰርዶ ከተማን ለመቆጣጠር ከታኅሣሥ 10/2014 ዓ.ም ጀምሮ በኪልበቲ ረሱ ዞን የህወሓት ኃይሎች ጦርነት መክፈታቸውን ዘርዝሯል፡፡

ይህ አዲስ ተጀምሯል የተባለውን ጦርነት በተመለከተ እስካሁን ከህወሓት በኩል የተባለ ነገር የለም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ከአፋር የተፈናቀሉ ሰዎች ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ነዋሪዎች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:43 0:00


XS
SM
MD
LG