በአማራ ክልል አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ለተባሉ ከ11 ሚሊዮን በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ በመንግሥትና በአጋር አካላት ድጋፍ፣ የምግብ እና መሰረታዊ ግብዓቶች እየተከፋፈሉ መሆኑን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባባሪያ ኮሚሽን አስታውቋል።
የዓለም ምግብ ፕሮግራምን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ለተፈናቃዮች ድጋፍ እያደረሱ ቢሆንም በክልሉ ከደረሰው ጉዳት ጋር ሲነፃፀር ግን ድጋፉ አነስተኛ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
በክልሉ በተለያዩ ምክንያት ተፈናቅለው አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው ውስጥ ከ700 ሺሕ የሚልቁት ምንም ዓይነት ድጋፍ እንዳላገኙም ኮሚሽኑ ጨምሮ አስታውቋል፡፡