በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምላሽ ያላገኙ የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች ድጋሚ ሰላማዊ ሰልፍ አካሔዱ


ምላሽ ያላገኙ የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች ድጋሚ ሰላማዊ ሰልፍ አካሔዱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:03 0:00

ምላሽ ያላገኙ የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች ድጋሚ ሰላማዊ ሰልፍ አካሔዱ

በትግራይ ክልል አራት ከተሞች የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ ዛሬ ባካሔዱት ሰላማዊ ሰልፍ፣ ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱና አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ እንዲቀርብላቸው ጠይቀዋል።

ይህንኑ ጥያቄአቸውን በተደጋጋሚ እንዳቀረቡ ለአሜሪካ ድምፅ ያስታወሱ ተፈናቃዮቹ፣ ምላሽ አለማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

ሰላማዊ ሰልፎቹ የተካሔዱባቸው ከተሞች፥ ዓዲ ግራት፣ ዓድዋ፣ ሽረ እንዳሥላሴ እና አኵስም ናቸው፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ይኹንና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ከዚህ ቀደም በሰጣቸው መግለጫዎች፣ የተፈናቃዮቹን ጥያቄ በፕሪቶርያው ስምምነት መሠረት ለመመለስ፣ ከፌዴራሉ መንግሥት ጋራ ተባብሮ እንደሚሠራ ገልጿል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG