በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለወገን ደራሹ የበጎ አድራጎት ድርጅት


ለወገን ደራሹ የበጎ አድራጎት ድርጅት
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:17 0:00

ለችግር የተጋለጡ ሕፃናትንና ቤተሰቦቻቸውን በመርዳት ሥራ ላይ የተሰማራ፣ “ወገኔ የኢትዮጵያውያን ማኅበር” የተሰኘ የበጎ አድራጎት ማኅበርን በአሁኑ ወቅት፣ በዐዲስ አበባ ከተማ ውስጥ፣ ለተለያዩ የቤተሰብ አባላት ድጋፎችን በማድረግ ላይ ይገኛል።

“ወገኔ የኢትዮጵያውያን ማኅበር” ከ23 ዓመታት በፊት በዩናይትድ ስቴትስ በሚኖሩ አሥር ኢትዮጵያውያን የተመሠረተ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡ “በብዙ ችግሮች ውስጥ የምትገኘውን የትውልድ አገራችንን በምን ልናግዝ እንችላለን?’ ብለን ስንወያይ ነው ሐሳቡ የመጣልን” ይላሉ፡ መስራቾቹ ስለወገኔ አመሰራረት ሲናገሩ።

ከዚያም በየወሩ ጥቂት ገንዘብ እያዋጡ፣ በአዲስ አበባ ጎዳና ላይ የሚገኙ ችግረኛ ቤተሰቦችን ማንሳት እንደጀመሩም ይገልጻሉ፡፡ “ወገኔ” በ23 ዓመታት ዕድሜው ከ800 በላይ ቤተሰቦችን ደግፏል፡፡

ከነዚህም ብዙዎች ራሳቸውን እንዲችሉ ከመርዳት በተጨማሪ፣ ልጆቻቸውንም አስተምሮ ለቁም ነገር አብቅቷል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ከ360 በላይ ለሚሆኑ ቤተሰቦች የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ 23ኛ ዓመቱን በዐዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል፡፡

ከዝግጅቶቹ በአንዳቸው ላይ የታደመው ዘጋቢያችን ያሰናዳውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG