የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከመጪው 2017 የትምህርት አመት ጀምሮ፣ ተማሪዎችን የሚቀበልበትን አዲስ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ማቀዱን አስታወቀ፡፡ የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፣ በዛሬው ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው የመንግስት ራስገዝ ከፍተኛ የትምሕርት ተቋም ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፣ በመጪው አመት በዩኒቨርሲቲው የሚማሩ ተማሪዎች በመንግስት የሚመደቡ ሳይሆኑ፣ በተቋም መስፈርት መሰረት የሚመለመሉ አመልክተዋል፡፡
ተማሪዎቹ፣ በራሳቸው ከፍለው የሚማሩ እና መክፈል የማይችሉ ተማሪዎች መንግስት የትምህርት ወጪያቸውን የሚሸንፍላቸው እንደሚሆኑም ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡ ይህንን አስመልክቶ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው አንዳንድ የከፍተኛ ትምሕርት መምሕራን ‘አሰራሩ በትክክል ከተተገበረ፣ ለትምህርት ጥራት መሻሻል አስተዋፅኦ የሚያደርግ ነው’ ይላሉ፡፡