በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰልፎች ውዝግብ በአዲስ አበባ


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የሰማያዊ ፓርቲ ውዝግብ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የሰማያዊ ፓርቲ ውዝግብ

የተለያየ ዓላማ የላቸው ሁለት ሰላማዊ ሰልፎች በተመሣሣይ ቁንና ሰዓት መስቀል አደባባይ ላይ ተጠርተዋል፡፡




please wait

No media source currently available

0:00 0:07:20 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የተለያየ ዓላማ የላቸው ሁለት ሰላማዊ ሰልፎች በተመሣሣይ ቁንና ሰዓት መስቀል አደባባይ ላይ ተጠርተዋል፡፡

ይህ የአዲስ አበባ አስተዳደርና ሰማያዊ ፓርቲ እየተወዛገቡበት ያለ ጉዳይ ነው፡፡

በሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የተጠራው አክራሪነትንና ፅንፈኝነትን የማውገዝ ዓላማ ያለው ሰልፍ የፊታችን ዕሁድ ነኀሴ 26/2005 ዓ.ም መስቀል አደባባይ እንዲካሄድ ፍቃድ መሰጠቱን የአዲስ አበባ አስተዳደር አስታውቋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ “በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ በቅድሚያ የጠየቅነው እኛ ነን፤ በማካሄድም እንገፋበታለን” ብሏል፡፡

“ይህ አባባል ሕገወጥና ዕብሪት ነው” ያለው የአዲስ አበባ አስተዳደር በበኩሉ “ቀድሞ ጥያቄ ያቀረበው የሃይማኖት ጉባዔ ነው” ብሏል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG