በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ክሥ ቀረበበት


የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ክሥ ቀረበበት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:00 0:00

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያዊው ባለሀብት አቶ ሳምሶን ተክለ ሚካኤል ጉዳይ መከሠሣቸውን፣ የባለሀብቱ የሕግ አማካሪ ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያዊው ባለሀብት አቶ ሳምሶን ተክለ ሚካኤል፣ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት፣ በኬንያ-ናይሮቢ በፖሊሶች ተይዘው ከተወሰዱ በኋላ እስከ አሁን የት እንዳሉ እንደማይታወቅ፣ ባለቤታቸው ወይዘሮ ሚሌን ሓለፎም ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ ሚሌን፣ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲን፣ ስለ ጉዳዩ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም፣ እስከ አሁን ምንም ዓይነት ፍንጭ አለማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ ባለሀብቱ ያሉበት ቦታ እና ኹኔታ እንዲታወቅ፣ እንዲሁም ፍትሕ እንዲያገኙ አላደረጉም በተባሉ አካላት ላይ ክሥ መመሥረቱንም የሕግ አማካሪያቸው ዶ/ር ዳባ ጩፋ ገልጸዋል፡፡

በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ክሥ የተመሠረተባቸው አካላትም፣ የኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ የኬንያ ኤምባሲ እንደኾኑ፣ ዶ/ር ዳባ ጠቅሰዋል፡፡

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ የሰብአዊ መብቶች ችሎት፣ ጉዳዩን ማየት መጀመሩንም የሕግ ባለሞያው ተናግረዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG