በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሠላሳ ሀገራት ብሪክስን ለመቀላቀል የአባልነት ጥያቄ ማቅረባቸውን ሩሲያ አስታወቀች


ሠላሳ ሀገራት ብሪክስን ለመቀላቀል የአባልነት ጥያቄ ማቅረባቸውን ሩሲያ አስታወቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:43 0:00

ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የመሠረቱትንና ብሪክስ እየተባለ የሚታወቀውን ዐዲስ ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ጥምረት ለመቀላቀል፣ ሠላሳ ሀገራት ጥያቄ ማቅረባቸውን፣ የሩሲያ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ኢጎር ሞሮዞቭ አስታወቁ፡፡

ሊቀ መንበሩ፣ በሩሲያ-አፍሪካ ግንኙነት ዙርያ በሚመክር አንድ መድረክ ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፣ የብሪክስ ጥምረት እነዚኽን ሀገራት ሲያካትት፣ የዓለምን ሁለት ሦስተኛ ገበያ ይቆጣጠራል፤ ብለዋል፡፡ ሀገራቱ ያቀረቡት የአባልነት ጥያቄ፣ ከአንድ ወር በኋላ ምላሽ እንደሚያገኝም፣ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቬግኒ ቴሬኪን ጠቁመዋል፡፡ በምክክር መድረኩ ላይ የተሳተፉ ሰዎች፣ ዐዲሱ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ጥምረት፣ ለአዳጊ ሀገራት የተለያዩ ጥቅሞችን ያመጣል፤ ይላሉ፡፡

የኢኮኖሚ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገዳ በበኩላቸው፣ “አዳጊዎቹ ሀገራት የጥምረቱ አባል በመኾናቸው ብቻ የሚያገኙት ቀጥተኛ ጥቅም የለም፤” ይላሉ፡፡

ሙሉ ዘገባን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG