በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምክር ቤት አባሉ ለስድስት ቀናት ያሉበት አልታወቀም


የምክር ቤት አባሉ ለስድስት ቀናት ያሉበት አልታወቀም
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:15 0:00

የምክር ቤት አባሉ ለስድስት ቀናት ያሉበት አልታወቀም

የአማራ ክልል ምክር ቤት እና የፌደሬሽን ምክር ቤት አባሉ አቶ ሀብታሙ በላይነህ፣ ካለፈው ሳምንት ዐርብ አንሥቶ፣ አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው እንደወጡ ሳይመለሱ መቅረታቸውን፣ የቅርብ ጓደኛቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

አቶ ሀብታሙ የፌዴሬሽን ምክር ቤትም አባል እንደሆኑ የገለጹት አስተያየት ሰጪው፣ ወደ ስብሰባው ከማምራታቸው በፊት ዐርብ ጠዋት አራት ኪሎ አካባቢ የሚገኘው ቢሯቸው ገብተው እንደነበርም አስታውሰዋል። ከረፋድ አምስት ሰዓት በኋላ ግን ስልካቸው መዘጋቱን ገልጸዋል። ከቀጣዩ ቀን ጀምሮ ከቤተሰቦቻቸው ጋራ እያፈላለጓቸው ቢሆኑም፣ እስከ አሁን ድረስ ያሉበትን ለማወቅ እንዳልቻሉ አመልክተዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG