በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዒድ አልፈጥር በዓል የስግደት ሥነ ስርዓት በአካባቢው በተፈጠረ ‘ረብሻ’ ምክንያት ተስተጓጉሏል


የዒድ አልፈጥር በዓል የስግደት ሥነ ስርዓት በአካባቢው በተፈጠረ ‘ረብሻ’ ምክንያት ተስተጓጉሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:39 0:00

የረብሻው ምክንያት ፖሊስ ባርቆብኝ ተኮስኩ ያለው አስለቃሽ ጭስ መሆኑን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አስታውቋል፡፡ ግርግሩ የተፈጠረውም በአንድ ፌዴራል ፖሊስ በድንገት በተተኮሰ አስለቃሽ ጭስ ምክንያት መሆኑን ገልጿል። የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሱልጣን ሃጂ አማን፣ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ከፖሊስና ከበጎ ፈቃደኛ አስተባብሪዎች ያገኙትን መረጃ አጣምረው ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በተፈጠረው ግርግርም የጠፋ የሰው ሕይወት እንደሌለም ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ ደግሞ ረብሻውን ያስነሱት ጥቂት ግለሰቦች እንደሆኑ እና በዚህም ምክንያት በንብረት ላይ ጉዳት እንደደረሰ አስታውቋል፡፡

በረብሻው ምክንያት በፀጥታ ኃይሎች ላይ ከደረሰዉ መለስተኛ ጉዳት ውጭ በሰው ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን መንግስት የገለጸ ሲሆን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤትም እስካሁን ሰው ስለመጎዳቱ መረጃ እንዳልደረሰው አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG