የውጭ ጣልቃ ገብነትንና ህወሓትን ያወገዙ ሠልፎች ዛሬ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ተካሂደዋል።
አዲስ አበባ ውስጥ የወጡ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ ሠልፈኞች በተጠራው የሠላም ንግግር ላይም ሀሳቦቻቸውን አካፍለዋል።
ከውጭ ጣልቃ ገብነት ጋር ተያይዞ የመንግሥቱ ደጋፊዎች የሚያነሷት የዩናይትድ ስቴትስ ክሶቹን ታስተባብላለች። በሌላ በኩል የህግ መወሰኛ ምክር ቤቷ የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሰብሳቢ ሴናተር ባብ ሜኔንዴዝ የባይደን አስተዳደር ኢትዮጵያን ለ18 ወራት ጊዜያዊ የከለላ ፈቃድ ዝርዝር ውስጥ ማስገባቱን አድንቀዋል።
[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]