ቢሮው በፖሊስ በመከበቡ ምክንያት መደበኛ የቢሮ ሥራ ማከናወን እንዳልቻለ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አስታወቀ።
“ድርጊቱ የዓድዋ በዓልን በተረጋጋ መልኩ እንዳናከብር ታስቦ እንደሚደረግ እናምናለን” ያሉት የፓርቲው ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ቀለብ ስዩም፣ ለዚህም ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ይደረግ ነበር ያሉትን የአባላት እስር በማሳያነት አቅርበዋል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ሊሳካልን አልቻለም፡፡
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።