"በኮምፒዩተር ተጠቅማ በኅብረተሰብ መካከል አመጽ፣ ሁከት እና ግጭት ለማነሳሳት ሞክራለች” በሚል የወንጀል ክስ ከሳምንት በፊት የ"ጥፋተኝነት" ውሳኔ የተላለፈባት “ኢትዮ ንቃት” የተሰኘ የዩቲዩብ ብዙኃን መገናኛ አዘጋጅ መስከረም አበራ፣ ለፍርድ ውሳኔ ለዛሬ ሐሙስ ተቀጥራ የነበረ ቢኾንም ዳኛ ባለመሟላቱ ለሦስተኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። በተያያዘ በእነ ዶ.ር. ወንድወሰን አሰፋ የክስ መዝገብ ሥር የሚገኙ የሽብር ተከሳሾችም ዛሬ ለፍርድ ቤቱ በሰጡት የእምነት ክህደት ቃላቸው የቀረበባቸውን ወንጀል አለመፈፀማቸውን ገልጸዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ቃል ለመስማት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
መድረክ / ፎረም