የኢትዮጵያዊያን ሙስሊም ማኅበረሰብን ጥያቄ እንወክላለን የሚሉት እነ አቡበከር አህመድ ሞሃመድ አቃቤ ሕግ ያቀረበባቸውን ክሥ ተቃወሙ።
ጉዳያቸው የቀረበለት ፍርድ ቤት የማየት መብት እንደሌለው ገለፁ።
በእነ አንዱዓለም አራጌና እስክንድር ነጋ የክሥ መዝገብም የይግባኝ አቤቱታ ቀርቧል።
በከፍተኛው ፍርድ ቤት በሽብር ፈጠራና ብሔራዊ ጥቅምን አሣልፎ በመስጠት ወንጀለኛ ያላቸውን ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተቃዋሚዎች አቤቱታ አቃቢ ህግ መልስ እንዲሰጥበት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በሌላ በኩል ለህሊና እስረኞች የሚሟገተው ፍሪደም ናው “Freedom Now” የሚባለው ድርጅት የእስክንድር ነጋን ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያላግባብ የታሠሩ ሰዎችን ጉዳይ ለሚያጠናው ግብረኃይል ማቅረቡ ታወቀ።
ግብረኃይሉ በቀረበለት መመልከቻ ላይ በመጭው ሚያዝያ ውሣኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
የድርጅቱን ሥራ አስኪያጅ ዘጋቢያችን መለስካቸው አምሃ አዲስ አበባ ላይ አነጋግሯቸዋል።
ዘገባዎቹን ያዳምጡ፡፡