በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ያልተፈለገ ፅንስን በጥንቃቄ ለማቋረጥ የሚያስችል አዲስ ዘዴ ተግባር ላይ ዋለ


የመቐለና የኣዲስ ኣባባ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ካሊፎርንያ ዩኒቨርሲቲ ስር ከሚገኘው VSI (Venture Strategies Innovations) መንግስታዊ ያልሆነ የጤና ድርጅት ጋራ በመተባበር ትግራይ ውስጥ ባካሄዱት ጥናት ያልተፈልገ እርግዝናን ለማስቀረት የሚረዳ ህክምናዊ ዘዴ ጀምረዋል።

የጥናቱ ውጤትም ግንቦት 9 (በኣውሮፓውያን ኣቆጣጠር) መቐለ ከተማ በተካሄደው ኣለም ኣቀፍ ሰሚናር ይፋ ተደርጓል።

ጥናቱ ትግራይ ክልል ውስጥ በመቐለ፣ በዓዲ ግራትና ዓብዪ ዓዲ በሚገኙ 4,400 እናቶች ላይ ባለፉት 18 ወራት የተካሄደ ሲሆን ውጤቱም የናቶች ሞትን ለመቀነስ የበለጠ ዘዴ ሆኖ መገኘቱን ሊቃውንቱ ገልጿል።

በጥናቱ ላይ የተሳተፉት የማህፀንና የፅንስ ከፍተኛ ሃኪም ዶ/ር ኣማኑኤል ገሰሰው “ኢትዮዽያ በኣውሮፓውያን ኣቆጣጠር በ2005 ዓ/ም በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ያልተፈለገ ፅንስ ማስወረድ ህጋዊ መሆኑን ተደንግጓል። በዚህም ህጉ ከመሻሻሉ በፊት ከህክምና ውጭና በቂ እውቀት በሌላቸው ሰዎች ይካሄድ የነበረውን ጥንቃቄ የጎደለው ፅንስ የማስወረድ ሂደት ቀርቷል። ይህ ደግሞ የእናቶች ሞት ከመቀነስ ኣንፃር ራሱን የቻለ ትልቅ ሚና ተጫውቷል”ብሏል።

ያልተፈለገ ፅንስን ለማስወረድ ወደ ሆስፒታል ይመጡ ከነበሩት እናቶች በኣመት ከ5-6 የሚሆኑት ሂወታቸው ያጡ እንደነበር ዶ/ር ኣማኑኤል በጥናቱ መሰረት ይናገራሉ። ኣሁን በተደረገው ክኒን በመስጠት የሚፈፀም ወርጃ ግን ኣደጋው በሚያስደንቅ ሁኔታ መቀነሱን ገልጿል።

ጥናቱ ትኩረት የሰጠበት ይህንን የህክምና ዘዴ በከፍተኛ ሃኪሞች ብቻ ሳይሆን ከሆስፒታል ኣልፎ በጤና ጣብያዎችና በጤና ኬላዎች ደግሞም በጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች የሚሰጥበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንደነበርም ባለሞያው ይናገራሉ።

ይህ በትግራይ ክልል ተካሂዶ ኣመርቂ ውጤት ያስገኘው ጥናት ሌሎች ክልሎችም ያላቸውን የጤና ድርጅቶች ኣወቃቀርና ኣጠቃላይ ያከባብያቸውን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ በወቅቱ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG