በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዐቢይ አህመድ በ"ታይም" ተመረጡ


ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ
ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከታይም መፅሔት መቶ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች አንዱ ሆነው ለ2019 ዕትሙ ተመረጡ።

ታይም መጽሔት በየዓመቱ የተጽዕኖ ፈጣሪዎች ዝርዝር ማውጣት ከጀመረ አሥራ ስድስተኛ ዓመቱ ሲሆን በዓለም ዙሪያ በመብቶች ተከራካሪነት፣ በፈጠራና በስኬት የተዋጣላቸው የሚላቸውን ሰዎች ከዓለም ዙሪያ ይሰይማል።

ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሆኑ ከሺህ በላይ የታይም ተመራጮች ከመንግሥትጽ፣ ከንግድ፣ ከመዝናኛ፣ ከጤና፣ ከስፖርትና ከሣይንስ ዘርፎች የታዩ ናቸው። ታይም የመጭ ትውልድ መሪዎች የሚላቸውንም በዚሁ የመቶ ተፅዕኖ አሣዳሪዎች ዝርዝሩ ያካትታል።

የተመራጮቹ ማንነት ከመቶ ሚሊየን በላይ ለሚሆነው የታይም መፅሔት ታዳሚና በሌሎችም መደበኛና የማኅበራዊ መገናኛዎች በዓለም ዙሪያ እንደሚገለፅ ታይም በዌብ ሳይቱ ላይ አስታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG