በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦብነጉ ቀልቢ ዳጋ ተለቀቁ


አብዲካሪም ሙሴ /ቀልቢ ዳጋ/ - የኦብነግ የጦር አዛዥ /ፎቶ ፋይል/
አብዲካሪም ሙሴ /ቀልቢ ዳጋ/ - የኦብነግ የጦር አዛዥ /ፎቶ ፋይል/

የኢትዮጵያ መንግሥት አሥሯቸው የቆዩትን የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር /ኦብነግ/ የጦር አዛዥ አብዲካሪም ሙሴን ዛሬ መልቀቁን የአካባቢውን አዛውንት ጠቅሶ የቪኦኤ ሶማሊኛ አገልግሎት ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግሥት አሥሯቸው የቆዩትን የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር /ኦብነግ/ የጦር አዛዥ አብዲካሪም ሙሴን ዛሬ መልቀቁን የአካባቢውን አዛውንት ጠቅሶ የቪኦኤ ሶማሊኛ አገልግሎት ዘግቧል።

ቀልቢ ዳጋ በሚል ተደራቢ ስም የሚታወቁት የኦብነጉ አዛዥ የተለቀቁት ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት መሆኑን ሡልጣን ፋውዚ ሞሐመድ አሊ የሚባሉ የታወቁ የሶማሌ ሽማግሌ ናቸው ለቪኦኤ የተናገሩት።

“ቀልቢ ዳጋ እንዲለቀቅ ፌደራል መንግሥቱ አዝዞ አሁን ያለው እኛ እጅ ላይ ነው” ብለዋል ሡልጣን ፋውዚ።

ቀልቢ ዳጋ በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና ሕይወታቸውንም እዚያው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚቀጥሉ የጠቆሙት ሡልጣን ፋውዚ ከኢትዮጵያ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው እንደሚነጋገሩም አመልክተዋል።

ቀልቢ ዳጋ ከተለቀቁ በኋላ አዲስ አበባ ላይ ከሶማሌ የሃገር ሽማግሌዎች ጋር ደስታቸውን ሲካፈሉ የሚያሳዩ ፎቶዎችን አሠራጭተዋል።

አብዲካሪም ሙሴን /ቀልቢ ዳጋን/ ባለፈው ነኀሴ ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፎ የሰጠው የሶማሌ መንግሥት እንደነበር መዘገቡ ይታወሣል።

በሌላ በኩል ግን ቪኦኤ ያነጋገራቸው የኦብነግ ቃል አቀባይ አብዱልቃድር ሃሰን ሂርሞጌ ስለቀልቢ ዳጋ መፈታት ግንባራቸው ገና የተረጋገጠ መረጃ እንደሌለው ጠቁመው “የኢትዮጵያ መንግሥት ለሃገር ሽማግሌ ሊሰጣቸው አይገባም ነበር፤ ስለደኅንነታቸው ኃላፊነት አለበት” ብለዋል።

ቀልቢ ዳጋ ዳዳብ-ኬንያ ከሚገኘው ቤተሰባቸው ጋር ቢቀላቀሉ ግንባራቸው እንደሚመርጥ ሂርሞጌ አክለው ተናግረዋል።

ተጨማሪ መረጃ ይዘን እንመለሣለን።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG