በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

Radio Magic




ጤና ይስጥልን፥

ሰላም፥

እንዴት ናችሁ?

ራዲዮ መጽሔቶች ነን፥ ከዋሽንግተን ዲሲ፤

አዝናኝና ቁም ነገር አዘል ብቻ ሳይሆኑ፤ ቀደም ሲል ያን ያህል ጎልተው ያልታዩ ትኩረት የሚጋብዙ ነጥቦችና አንዳች ጠያቂ ስሜት በውስጣችን የሚያጭሩ ቅንብሮች ጭምር የሚስተናገዱበት ፕሮግራም ነው -- የራዲዮ መጽሔት።

ሰዓት?

በልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ዘርፎች የተካኑ አንጋፋና ወጣት ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች በማራኪ ወጎቻቸውን ሊያስደምሙንና በጥበብ ሥራዎቻቸው ሊያዝናኑን ጭምር ቀጠሮ የሚይዙበት የሳምንቱ-መጨረሻ ልዩ ጊዜ፤ እሁድ ምሽት ነው ሰዓቱ።

የት?

በተለያዩ ርዕሶች ላይ ያተኮሩ ቃለ ምልልሶች፥ ለዛና ቁምነገር ያዘሉ አዝናኝ ወጎች፥ ሥነ ግጥምና ግሩም ዜማዎች፤ በአጠቃላይም ከጥሩ ራዲዮ ፕሮግራም መስማት የሚሿቸው ቀልብ-ገዢ ዝግጅቶች የሚደመጡበት የእርስዎ ራዲዮ -- የሰንበት ምሽት ምርጫዎ የራዲዮ መጽሔት ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።

የፕሮግራሙ አዘጋጆች፥ አዲሱ አበበና አሉላ ከበደ፤ የአዲስ አበባውን የራዲዮ መጽሔት ልዩ ዘጋቢያችንን ንጉሴ አክሊሉን ይዘን በየአስራ አምስት ቀኑ እሑድ ለዕለቱ በተለይ ከተሰናዱና ከተመረጡ ዝግጅቶቻችን ጋር ብቅ እንላለን።

አትጥፉ።

አዎን! እሑድ ከሆነ ዕለቱ፥
የራዲዮ መጽሔት ነው ሰዓቱ
አንዱን ዘሎ በሳምንቱ፤

A compelling radio program broadcast in Amharic from Washington, D.C.

Lively conversations with the best and the brightest, veterans and the upcoming stars among the nation's singers, musicians, lyricists, poets, writers, artists and others.

Radio that entertains, informs and engages. Radio that puts a smile on your face.

Join with hosts Addisu Abebe and Alula Kebede from the Voice of America’s studio 14 in Washington, D.C. and regular contributor Negussie Aklilu from Addis Ababa -- every other Sunday from 9:00 - 10:00pm for an hour of enjoyable listening.

Radio that makes a difference. A radio magazine from the Voice of America.

XS
SM
MD
LG