በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአብአላ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ተመለሱ


የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሠላማዊት ካሣ
የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሠላማዊት ካሣ

ህወሓት በአብአላ በኩል በከፈተው ጥቃት ምክንያት ለትግራይ ሕዝብ ሰብዓዊ ዕርዳታ ይዘው ወደ መቀሌ እየተጓዙ የነበሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ኋላ መመለሳቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አሰታወቀ።

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሠላማዊት ካሣ ማምሻውን ለአሜሪካ ድምፅ እንዳሉት ህወሓት ጥቃት የከፈተዉ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት በአካባቢው በሌለበት ሁኔታ ነው ብለዋል።

ጉዳዩን አስመልክቶ ቀደም ሲል በትዊተር ገፃቸው ላይ የጻፉት የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው "ከሰመራ ታጅበው ወደ ትግራይ ሊገቡ ነበር" ተብሎ የተነገሯቸው ሰብአዊ ዕርዳታ የጫኑ የዓለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም 27 የጭነት መኪኖች ወደ መቀሌ እንዳይገቡ ተደርገዋል ብለዋል።

በሌላ በኩል የህወሓት ኃይሎች በስድስት የአፋር ግምባሮች ከትናንት ጀምረው ከባድ ጦርነት መክፈታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ አስተያየታቸውን የሰጡ የአፋር ክልል ነዋሪ ገልፀዋል።

ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ከአብአላ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ተመለሱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:50 0:00


XS
SM
MD
LG