በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጎባኤው ቀዳሚ አጀንዳ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጻሚዎቹ ይሆናሉ


ፎቶ ፋይል፦ የሰብዓዊ መብት ጉባኤ
ፎቶ ፋይል፦ የሰብዓዊ መብት ጉባኤ

የዜጎቻቸውን የሰብዓዊ መብት በመጣስና ነፃነታቸውን በመንፈግ በተከሰሱ አገሮች ላይ፣ 47 አባላት ያሉት የሰብዓዊ መብት ጉባኤ፣ በሚቀጥሉት ሶስምት ሳምንታት ውስጥ በሚያደርገው ስብሰባ ከፍተኛ ምርመራና ግምገማ እንደሚያደርግባቸው ይጠበቃል፡፡ በስብሰባው ላይ እንደሚነሱ ከሚጠበቁት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል የቪኦኤ ዘጋቢ ሊሳ ሽላይን ከጄኔቫ ዘገባ አላት፡፡

ጉባኤው ሥራውን ሲጀምር በቅድሚያ የሚያደርገው፣ በአባል አገራቱ የሚቀርብለትን ወቅታዊውን የቤላሩስ ሁኔታና፣ በዚያ እየተፈጸመ ስላለው የሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ፣ የሚደረገውን አጣዳፊ ክርክር በማድመጥ እንደሆነ ይጠበቃል፡፡ እኤአ ነሀሴ 9 ቀን የተደረገውን፣ አወዛጋቢና ተጭበርብሯል የተባለውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን ተከትሎ፣ ሃገሪቱ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ገብታለች፡፡ በፊሊፕሊንስ፣ ፕሬዚዳንት ሮድሪጎ ዱተሬት፣ በአደንዛዥ እጽ ላይ ባወጁት ጦርነት ሳቢያ፣ ያለፍትህ የተገደሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ጉዳይም አንዱ መነጋገሪያ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚያም በተጨማሪ፣ ሊሎችም በዓመቱ ውስጥ የተከሰቱ ዋና ዋና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችም ይታያሉ፡፡ በሶሪያ፣ ማይናማር፣ ቬንዙዌላ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሊቢያ፣ ኢራን እና ካምቦዲያ በመሳሰሉ አገሮች የተፈጸሙ ግድያዎች፣ ግርፋት፣ ማሰቃየት፣ በዘፈቀደ የሚደረጉ እስራቶች፣ የሰዎችን ደብዛ ማጥፋትና ወሲባዊ ጥቃቶች መፈጸምን ጨምሮ፣ ሌሎች በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በዝርዝር ቀርበው የሚታዩበትም ጉባኤ ይሆናል፡፡

የዚያኑ ያክል፣ ቀደም ሲል ለጉባኤው ተሰጥተው የነበሩ አንዳንድ ሥልጣኖችም የሚያበቁበት ጊዜ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ከአራት ዓመት በፊት በብሩንዲ የተከሰተውን የሰአብዊ መብት ጥሰት ለመመርመር፣ ኃላፊነት የተሰጠው የሰአብዊ መብቱ ጉባኤው አጣሪ ኮሚሽን የማጠናቀቂያ ሪፖርቱንም የሚያቀርብበት ጊዜ በዚህ ወር መጨረሻ ይሆናል፡፡

ይሁን እንጂ በጄኔቫ የሰብአዊ መብት ተመልካቹ ድርጅት ዳይሬክተር ጆን ፊሸር ግን ለኮሺሚሽኑ የተሰጠው ሥልጣን አሁንም ተጠብቆ የሚቆይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ምክንያቱም በብሩንዲ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ፣ አሁንም አልተቀየረም፡፡ ምንም እንኳ ፕሬዚዳንት ኢቫሪስት ንዳዪሽማዬ፣ የረጅም ጊዜ የብሩንዲ ፕሬዚዳንት የነበሩትን ፕዬሬንኩሩንዚዛን ተክተው ፕሬዚዳንት ቢሆኑም ስጋቱ ግን አሁንም እንዳለ ነው፡፡

ፕሬዚዳንቱ ሰለ ሲቪል ማህበረሰቡ የሰጡት ማሳሰቢያ አስግቶናል፡፡ የውጭ አገር መንግሥታት መልእከተኛ መሆን ወይም ሚስጥር እያሾለኩ የሚሸጡ ወይም የሚያጋልጡ መሆን የለባቸውም ብለዋል፡፡ ያ የማህበረሰቡ አባላት መንግሥትን ከተመተቸት እንዲቆጠቡ ሊያደረጋቸው ይችላል፡፡

ፊሸር እንደሚሉት፣ በፕሬዚዳንት ንኩሩንዚዛ ዘመን ለነበረው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ተጠያቂ የነበሩት ባለሥልጣናት፣ አሁንም ሥልጣን ላይ ናቸው፡፡ የሰብአባዊ መብት አክቲቪስቶች፣ በዚኛው ጉባኤ፣ ጨርሶ የማይነኩ ናቸው የሚባሉ አገሮች ጉዳይ ጭምር እንዲታይ፣ ግፊት እያደረጉ ነው፡፡ እነዚህ ሃገሮች፣ ከፍተኛ አቅም ያላቸው በመሆኑ፣ ጉዳያቸው በሰአብዊ መብት ጉባኤ ፊት ቀርቦ አያውቅም፡፡ 321 የሚደርሱና ከ60 አገራት የተውጣጡ የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች፣ ቻይና እጅግ በተቀነባበረ መንገድ ትፈጽመዋለች ባሉት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ፣ ምርመራ እንዲካሄድ ጠይቀዋል፡፡ ራሺያም እንዲሁ፣ በቅርቡ በሶቭየት ህብረት ዘመን በነበረው የመግድያ መርዝ በመጠቀም፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ መሪ የሆነውን አሌክሲ ናቫልኒን መርዛ ለመግደል ሞክራለች፣ በማለት በጉባኤው እንዲታይ የጠየቁም አክቲቪስቶች አሉ፡፡

ፊሸርም እንዲሁ በሳኡዲ አረብያ እየተፈጸመ ያለው ጥሰትም ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ስለሴቶች መብት የሚሟገቱ የሰብአዊ መብት ታጋዮችና መንግስትን የሚተቹ ዜጎች በተለያየ መንገድ ታስረው ይገኛሉ፡፡ የእስር ቤቶች መጨናነቅ መኖሩና በተለይም በዚህ የኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት የጤና ቀውስ ስለመፈጠሩም ዝርዝር መረጃዎች ደርሰውናል፡፡ የህክምና እርዳታ እንዳይገኙ ተከልክለው ግልጽ ባለሆነ ሁኔታ የሞቱ እስረኞች መኖራቸውም ይታወቃል፡፡

ድሬክተሩ ጆን ፊሸር፣ ሳኡዲ አረብያ እሰረኞችን እንድትፈታ፣ የእስርቤቶችም ሁኔታዎች ላይ ማሻሻያ እንድታደርግ ግፊት ከማድረግ ጋር፣ ሃገሪቱን በሰአባዊ መብት ክትትል እይታ ሥር ማድረግ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የጎባኤው ቀዳሚ አጀንዳ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጻሚዎቹ ይሆናሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:22 0:00


XS
SM
MD
LG