በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁከተኛ ፅንፈኝነትን የመጋፈጫ ስብሰባ ተካሄደ


“...ዩናይትድ ስቴትስ ከእሥልምና ጋር ጦርነት ላይ አይደለችም...” ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፡፡
ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

please wait

No media source currently available

0:00 0:04:48 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ዩናይትድ ስቴትስ “…ከእሥልምና ጋር ጦርነት ላይ አይደለችም…” ብለዋል ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፡፡

“ሁከተኛ ፅንፈኝነትን መዋጋት” በሚል ርዕስ ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ባዘጋጀው የሁለት ቀናት ዓለምአቀፍ ገባዔ ላይ ንግግር ያደረጉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት - የእርሣቸው ሃገርና አውሮፓ በአንድ ወገን፤ በሌላ ደግሞ እሥልምና ትንቅንቅ ውስጥ የገቡ የሚያስመስልን አስተሳሰብ ውድቅ አድርገዋል፡፡

እንዲህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ፅንፈኞቹ ወጣት አሜሪካዊያንና ሌሎችንም ለማነሳሳትና ለሁከት ለማሰለፍ ጉዳይ እንዲመለምሉ መሣሪያ እየሆናቸው እንደሆነ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ከእሥልምና ጋር ትንቅንቅ ውስጥ እንዳለች አስመስሎ የሚቀርብ ማንኛውም ሃሣብ “አስቀያሚ ውሸት” ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርጆን ኬሪ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርጆን ኬሪ

ፕሬዚዳንቱ በሁከተኛ አክራሪነት ላይ ለሚመክረው ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ላዘጋጀው ዓለምአቀፍ ስብሰባ ተሣታፊዎች በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ከእሥላማዊ መንግሥት ቡድንና ከሌሎችም የሽብር ቡድኖች ጋር የሚያደርጉትን እፎይታ አልባ ፍልሚያ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ዝተዋል፡፡

በአመዛኙ እሥላማዊና አይሁድ የምዕራብ መንግሥታት በእሥልምና ላይ ጦርነት እያካሄዱ የሚያስመስልን ማንኛውንም ሃሣብ ፕሬዚዳንት ኦባማ በፅኑ ተቃውመዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

አስተያየቶችን ይዩ (1)

XS
SM
MD
LG