በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ የተፈናቃዮች ጉዳይ አማካሪ ሶማሊያን ጎበኙ


ፎቶ ፋይል፦ የስደተኞች ጣቢያ ዶሎ፣ ሶማሊያ 09/19/2022
ፎቶ ፋይል፦ የስደተኞች ጣቢያ ዶሎ፣ ሶማሊያ 09/19/2022

የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን በተመለከተ መፍትሄ ለመሻት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ አማካሪ ሆነው የሚያገለግሉት ሮበርት ፓይፐር የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን በሶማሊያ ትናንት አድርገው ከመንግሥት ባለሥልጣናትና ከተፈናቃዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

አማካሪው ወደ ሶማሊያ ያቀኑት ተፈናቃዮችና አጋር ደርጅቶች ያሉበትን ሁኔታ ለመረዳት እንዲሁም የተመድ እየሰጠ ያለው እርዳታ ምን እንደሚመስል ለማየት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሶማሊያ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ለመርዳት በተመድ በሚካሄደው ፕግራም ከታቀፉት 16 የተመድ አባል አገራት አንዷ ነች፡፡

ፕሮግራሙ ተፈናቃዮች ዘላቂ መፍትሄ እንዲሁም ከለላና እርዳት የሚያገኙበትን መንገድ የሚሻ ነው፡፡

በሶማሊያ ለአሥርት ዓመታት የተካሄደው ግጭትና ሁከት እንዲሁም በቅርቡ የተከሰተው ድርቅ ዜጎቿን ለተፈናቃይነት ዳርጓል፡፡

ሮበርት ፓይፐር በሶማሊያ ቆይታቸው ከሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ ጋር መንግሥታቸው ተፈናቃዮችን ለመርዳት ሥላለው ውጥንና የችግሩን ምንጭ ለማድረቅ የሚያደረገውን ጥረት በተመለከተ ተወያይተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG