በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ ምርጫ


የድምፅ ቆጠራ
የድምፅ ቆጠራ

በሩስያ ዜና በክሬምሊን ቤተ መንግሥት የሚደገፈው የተባበረው የሩስያ ፓርቲ በታችኛው ምክር ቤት አባላት ምርጫ ሁለት ሶስተኛውን ድምፅ አሸንፌያለሁ ሲል ተናገረ።

ለሦስት ቀናት የተካሄደው ድምፅ አሰጣጥ የተዛባ እና የማጭበርበር አድራጎት ተፈጽሞበታል ብለው ተቃዋሚዎች ቅሬታቸውን እያሰሙ ናቸው።

ምርጫው ለሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን እአአ በ2024 በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከተወዳደሩ ከወዲሁ ሥልጣናቸውን ለማጠናከር የያዙት ጥረት ትልቅ አካል መሆኑን ብዙዎች እየተናገሩ ናቸው። ለዚህ ደግሞ የመምሪያውን ምክር ቤት ዱማውን መቆጣጠር ቁልፍ እርምጃ መሆኑ ተጠቁሟል።

XS
SM
MD
LG