በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቱርክ ላይ የሩስያ እና የዩክሬን ሚኒስትሮች ስብሰባ ያለሥምምነት አበቃ


የዩክሬን እና የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቱርክ ጋባዥነት ሲወይዩ እአአ መጋቢት 10/2022
የዩክሬን እና የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቱርክ ጋባዥነት ሲወይዩ እአአ መጋቢት 10/2022

የዩክሬን እና የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ በቱርክ ጋባዥነት ተወያይተዋል። ሩሲያ በጎረቤትዋ ዩክሬይን ላይ ሙሉ ወረራ ከፈጸመችበት ጊዜ አንስቶ በሁለቱ ሃገሮች በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ የተደረገ የመጀመሪያ ውይይት ነው።

ሆኖም 90 ደቂቃዎች ከፈጀው ውይይት በኋላ ሁለቱም ወገኖች አንዳች ለውጥ አምጭ ከሆነ ሥምምነት ላይ ያለመደረሱን ተናግረዋል።

የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚትሮ ኩሌባ ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ለ24 ሰዓታት የተኩስ አቁም ስለማድረግ ቢወያዩም ሥምምነት ላይ ግን ያለመድረሳቸውን ነው ያስረዱት።

XS
SM
MD
LG