በሰሜን ናይጄሪያ ቦርኖ እስላማዊ ጽንፈኞች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ ሰባት ሰዎችን መግደላቸውን ነዋሪዎች አስታስወቁ፡፡
ግድያው የተካሄደው የተባበሩት መንግሥታ ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጎተሬዥ በጅሃድ ጥቃት በህይወት የተረፉት ሰዎች ለመጎብኘት በግዛቲቱ በተገኙበት ወቅት መሆኑ ተነግሯል፡፡
የተባበሩት መንግሥታ ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጎተሬዥ እንዲህ አሉ፣
"ለሰላም ማድረግ የምንችለው ነገር እጅግ ተስፋ አጥተው በጨነቃቸው ጊዜ ወደ ሽብርተኝነት የተየቀሩትና አሁን ግን ተመልሰው ሰላማዊ ዜጎች በመሆን ለወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ደህንነት አስተዋፆኦ ማበርከት የሚፈልጉትን መልሶ ማቀፍ ነው፡፡"
ናይጄሪያ ከአስርት ዓመታት በላይ የቦኮኻራም አማጽያንና በአቅራቢያዋ የሚገኙትን የምዕራብ አፍሪካ የእስላማዊ መንግሥት አማራጆችን ስታዋጋ ቆይታለች፡፡
የተባበሩት መንግሥታት በአክራሪዎቹ ጥቃት ከ35ሺ ሰዎች በላይ የተገደሉ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውን አስታውቋል፡፡