በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናሳው ቴሌስኮፕ ምስሎችን ማሰተላለፉን ቀጥሏል

የዩናይትድ ስቴትስ የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ፣ ጄምስ ዌብ ቴሌስኮፕ በተባለው የጠፈር መመልከቻ መሳሪያው የመጀመሪያውን የተሟላ የባለቀለም ምስል ማሳየት ቀጥሏል፡፡ 

ለመጀመሪያ ጊዜ በህዋው ላይ የሚገኙ ከዋክብትና ጋላክሲዎችን ጨምሮ ጥልቅ የአጽናፍ ገጽታዎችን ያሳየው ናሳ የተሟላውን ምስል መልቀቅ የጀመረው ባለፈው ማክሰኞ ነው፡፡

ፕሬዚዳን ጆ ባይደን “በአጽናፈ ዐለም (ዩኒቨርስ) ታሪካችን አዲስ መስኮት ነው” ብለውታል፡፡

10 ቢሊዮን ዶላር ያወጣው መመልከቻው ቴሌኮስፕ እስከዛሬ ወደ ጠፈር ከተላኩት ሁሉ ትልቁና ወደ ህዋው አጽናፍ ርቆ በመዝለቅ ዐቅሙ ወደር የሌለው መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ቴሌስኮፑ ወደ ጠፈር የተወነጨፈው እኤአ ታህሳስ 25 ደቡብ አሜሪካ ከሚገኘው የፍሬንች ጋያና ጣቢያ ሲሆን፣ ወደ ታች ወደ ምድር ምስል ከማቀበሉ በፊት፣ ከምድር 1.6 ሚሊዮን ኬሎሜትሮች ርቆ መጓዙ ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG