ባለፈው ቅዳሜ የተፈጸመው ጥቃት ስልጣን ላይ ያለው በጦር ሰራዊቱ የሚመራ መንግሥት ቢሆንም የጸጥታው ሁኔታ እየተባባሰ መሆኑን የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል። የጸጥታ ተንታኞች በክልሉ ከሁሉም የከፋ ሁከት ላይ ካለችው ከማሊም የባሰ ሁኔታ ላይ እንዳለች ተናግረዋል።
ታጣቂዎች ባለፈው ቅዳሜ በቡርኪና ሰሜናዊ አካባቢ በሚገኝ መንደር ግድያውን እንደፈጸሙ የሀገሪቱ መንግሥት አስታውቋል።
በወታደራዊ መንግሥት በሚተዳደሩት በቡርኪና ፋሶ እና በማሊ ሁከቱ ተባብሶ ቀጥሏል።