በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን መብት ተሟጋች ሞቶ ተገኘ


ናይሮቢ፣ ኬንያ
ናይሮቢ፣ ኬንያ

በኬንያ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን (የኤልጂቢቲ) የመብት ተመጓች አስክሬን በምዕራብ የአገሪቱ ክፍል ኡሲን ጊሹ ወረዳ በብረት ሳጥን ተደርጎ ከመንገድ ዳር ተጥሎ መገኘቱን ተነገረ።

አስክሬኑ የተገኘው በሞተር ብስክሌት የታክሲ አገልግሎት የሚሰጥ አንድ ሰው፣ የሰሌዳ ቁጥር የሌለው አንድ ተሽከርካሪ ሳጥኑን ከመንገድ ዳር ሲጥል መመልከቱን ለፖሊስ በማስታወቁ ነው ሲል የዛሬው የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል።

ፖሊስ ኤዲዊን ቺሎባ የተባለውን ግለሰብ አስክሬን በሳጥን ውስጥ ማግኘቱን አስታውቋል። የግድያው መንስኤና ዓላማ አለመታወቁን ዘገባው አመልክቷል።

ኬኒያ የተመሳሳይ ወንዶች መካከል የሚካሄድን የጾታ ግንኝነት የምትወነጅል ሲሆን ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘን እስከ አስራት ዓመት ድረስ በእስር ትቀጣለች ሲል የዓለም አቀፍ የኤልጂቢቲ( LGBT) ሰዎች መብቶች ተሟጋች የሆነው የሰዎች ክብርና ዕምነት (Human Dignity Trust) የተባለው የድርጅት አስታውቋል።

ድርጅቱ ጨምሮ እንዳስታወቀው ኬንያ ውስጥ በቅርብ ዓመታት ውስጥ “ካኩማ በተባለው የፍልስተኞ ጣቢያ ውስጥ ታዋቂ በሆኑ የLGBT ፍልሰተኞች ላይ ተከታታይ የሆነ መድልኦና ጥቃቶች ይፈጸማሉ” ብሏል።

XS
SM
MD
LG