በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትሯ ላይ የሞት ቅጣት አሳለፈች


ፎቶ ፋይል፦ የኢራን የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትር ዓሊሬዛ አክባሪ
ፎቶ ፋይል፦ የኢራን የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትር ዓሊሬዛ አክባሪ

የእንግሊዝና የኢራን ጥምር ዜግነት ያላቸው የኢራን የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትር ላይ ለእንግሊዝ ሰልለዋል በሚል አገሪቱ የሞት ቅጣት አስተላልፋለች።

እንግሊዝ በበኩሏ በዓሊሬዛ አክባሪ ላይ የተላለፈው የሞት ቅጣት ፖለቲካዊ መሆኑንና በአስቸኳይ እንዲለቀቅ ጠይቃለች።

ዓሊሬዛ አክባሪ የኢራን የበላይ ብሔራዊ የፀጥታ ም/ቤት ፀኃፊ የሆኑት አሊ ሻምካኒ የቅርብ ሰው ሲሆኑ በእርሳቸው ሥር ከእ.አ.አ 1997 እስከ 2005 ድረስ በመከላከያ ሚኒስትርነት አገልግለዋል፡፡

“የእንግሊዝ የሥለላ ተቋም በኢራን ካለው እጅግ ጠቃሚ ወኪሎች አንዱ ሲሆኑ፣ በአገሪቱ የተለየ ጥበቃ የሚደረግላቸው ተቋሞች ውስጥ መግባት መውጣት የሚችሉ ነበሩ” ብሏል የኢራን ያገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫው።

“አክባሪ ሆን ብሎ እያውቀ ለጠላት የሥለላ ተቋም መረጃ ይሰጥ ነበር” ሲል አክሏል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ።

የእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጄምስ ክሌቨርሊ አክባሪ እንዲለቀቅ ጥሪ አድርገዋል።

“ይህ ለሰው ሕይወት ደንታ በሌለው ጠካኝ አገዛዝ የቀረበ ፖለቲካዊ ክስ ነው። ኢራን የሞት ቅጣቱን ተፈጻሚ ማድረግ የለባትም” ብለዋል ክሌቨርሊ በትዊተር መልዕክታቸው።

የኢራን ጠቅላይ ፍ/ቤት የአክባሪን የሞት ቅጣት አጽንቷል፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በፈርንሣይ የሚገኝ አንድ ከተማ የኢራኑን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ ሩሆላ ኻሚኒ ፎቶ የያዘን ምልክት ለመደበቅ ወስኗል።
ከፓሪ ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘውና ኖፍለ-ለ ሻቱ በተሰኘችው ከተማ የሚገኘው የአያቶላ ፎቶ እንደሚሸፈን የከተማዋ ከንቲባ ተናግረዋል።

አሁን በኢራን እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ ምክንያት መንግስት ራሱን ከአያቶላው እንዲያርቅ 40 የሚሆኑ ቡድኖች በመጠየቃቸው ነው ተብሏል።

አያቶላው በ እ.አ.አ 1978 እና 1979 ላይ ወደ ኢራን ከመመለሳቸው በፊት በዛ በድንጋይ በተሠራው ትልቅ የገጠር ቤት ውስጥ፣ ፍረንሣዮቹ ሻቱ ይሉታል፣ ኖረው ነበር።

XS
SM
MD
LG