በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጥምቀት በጎንደር


ከተራ በጎንደር
ከተራ በጎንደር

የከተራ በዓል ቁጥሩ “እጅግ የበዛ” የተባለ ምዕመንና ታዳሚ በተገኘበት ጎንደር ላይ በድምቀት እየተከበረ ነው።

ሰሞኑን ከየሃገሩ ወደ ትውልድ ሃገራቸው የገቡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ በሰፋ ቁጥር መገኘታቸውም ለበዓሉ የተለየ ድምቀት እንደሰጠው የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጭዎች ገልፀዋል።

የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከተካሄደባቸው አካባቢዎች አቅራቢያ የምትገኘው “የጎንደር የሰሞኑ ድባብ ሁኔታዎች እየተቀየሩ መሆናቸውን ያሳያሉ” ሲሉ ተስፋቸውን የገለፁም አሉ።

በበዓሉ የሚሳተፉ መንገደኞችን ለማጓጓዝ የበረራዎቹን ቁጥር የጨመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ብቻ ወደ ጎንደር 23 በረራዎችን ማድረጉን ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል።

የዛሬው የጎንደር በረራዎች ቁጥር በአንድ ቀን ወደ አንድ መዳረሻ የተደረገ ከፍተኛው የበረራዎች ቁጥር በመሆን ክብረ ወሰን የተመዘገበበት መሆኑንም አየር መንገዱ አመልክቷል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።

ጥምቀት በጎንደር
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:21 0:00


XS
SM
MD
LG