በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሴቶች ቀንንን በማስመልከት ሙሉ በሙሉ በሴቶች የተመራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቡድን በዋሺንግተን ዲሲ


የዓለም የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የተመራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ  የበረራ ቡድን በዛሬው ዕለት ወደ ዮናይት ስቴትስ የተሳካ በረራ አድርጓል። የዋሺንግተን ዲሲ ከንቲባ ተወካይ፣የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይ እና የአየር መንገዱ ባለስልጣናት ይሄን ልዩ ቀን ምክንያት አድርገው ባስተላለፉት መልዕክት-የዛሬው በረራ ሴቶች በማናቸውም የስራ ዘርፎች ውስጥ የላቀ ሚና መጫወት እንደሚችሉ ማሳያ አድርገው አውስተውለታል።

የዓለም የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የተመራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቡድን በዛሬው ዕለት ወደ ዮናይት ስቴትስ የተሳካ በረራ አድርጓል።

በካፒቴን አምሳለ ጓሉ አብራሪነት ከአዲስ አበባ የተነሳው አውሮፕላን በዋሺንግተን ዳላስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በደረሰበት ወቅት ሞቅ ያለ አቀባበል ጠብቆታል።

የዋሺንግተን ዲሲ ከንቲባ ተወካይ፣የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይ እና የአየር መንገዱ ባለስልጣናት ይሄን ልዩ ቀን ምክንያት አድርገው ባስተላለፉት መልዕክት-የዛሬው በረራ ሴቶች በማናቸውም የስራ ዘርፎች ውስጥ የላቀ ሚና መጫወት እንደሚችሉ ማሳያ አድርገው አውስተውለታል።

አየር መንገዱ በአብራሪነት፣በበረራ መስተግዶ፣ በበራራ ምህንድስና እና መሰል ዘርፎች ሙሉ በሙሉ ሴቶች የተሳተፉበት በረራ ሲያደርግ ይሄ ለስድስተኛ ጊዜ ነው።

XS
SM
MD
LG