በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኅዳሴ ግድብ ግንባታ በሁለት ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ


የኅዳሴ ግድብ ግንባታ በሁለት ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:00 0:00

ሁለተኛው እና 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው የኅዳሴ ግድብ ተርባይን የኤሌክትሪከ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ዛሬ ይፋ ተደረገ። አጠቃላይ ግንባታው በሁለት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

ሦስተኛው ሙሌት በሂደት ላይ መሆኑን የገለጹት የኅዳሴ ግድቡ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ በሁለት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የግድቡን ሁለተኛ ዩኒት የኤሌክትሪከ ኃይል ማመንጫ ሥራ ያስጀመረችው ከአባይ ተፋሰስ የግርጌ ሃገሮች ማለትም ግብጽ እና ሱዳን ጋር ያላት አለመግባባት ተባብሶ በቀጠለበት ወቅት ነው፡፡

ኢትዮጵያ ከእነዚህ ሃገሮች ጋራ ስምምነት ላይ ሳትደርስ ኅዳሴ ግድብን ለሦስተኛ ጊዜ መሙላት ልትጀምር ነው ስትል ግብፅ በቅርቡ ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ተቃውሞ ማቅረቧን ይታወሳል።

በአፍሪካ አቻ የሌለው ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ይሆናል የተባለው ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ግንባታ በተለይ በኢትዮጵያና በሁለቱ የግርጌ ሃገሮች መካከል የውጥረትና የንትርክ ሰበብ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።

ዛሬ ሁለተኛውን የኅዳሴ ግድብ ተርባይ የኤሌክትሪከ ኃይል ማመንጫ መርቀው የከፈቱት

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሀገራቸው የታችኛውን ተፋሰስ ሀገራት የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላት ገልጸው፣ ከውይይት ውጭ የሚወሰድ እርምጃ ማንንም እንደማያዋጣ ተናግረዋል።

የዛሬ አሥራ አንድ ዓመት የተጀመረው ከአራት ቢሊዮን ዶላር የሚፈጀው የኅዳሴ ግድብ ግንባታ ሲጠናቀቅ 5000 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ ይጠበቃል።

XS
SM
MD
LG