በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግብጽና የኢትዮጵያ ድርድሮችና ውዝግቦች


Grand Ethiopian Renaissance Dam
Grand Ethiopian Renaissance Dam

ለወራት ተቋርጦ የነበረውና ለሳምንት የዘለቀው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የአዲስ አበባ ድርድር ያለ ስምምነት መቋጨቱን ተከትሎ በተለይ ግብጽ እና ኢትዮጵያ ሊሰውዷቸው የሚችሉ አማራጮች እያነጋገሩ ነው።

እንደ ቀደሙት ሁሉ በመሰንበቻውም የሶስቱ የተፋሰሱ አገሮች ድርድር - ሁለቱ አገሮች ኢትዮጵያ እና ግብጽ ከሁነኛ ስምምነት ለመድረስ ፍቃደኛ አልሆነም ሲሉ አንዱ ሌላውን በአደናቃፊነት ይወነጅላሉ።

ኢትዮጵያ በመጭው ጥቂት ሳምንታት ውስጥ እንደምታካሂድ ይፋ ያደረገችውን ዕቅድ ተከትሎም የግራ ቀኝ ውዝግቡ አይሏል። በአንጻሩም ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማድረግ የያዘችውን ግፊት አጠናቅራ መቀጠሏ ተዘግቧል። በሌላ በኩል በድርድሮቹ በአንዳንድ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት መደረስ መቻላቸውም ተጠቁሟል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የድርድሮቹን አካሄድና በቀጣናው የጸጥታ ጉዳዮች ላይ የሚኖረውን አንድምታ የገመገመው ዓለም አቀፉ የግጭቶች አስወጋጅ ቡድን International Crisis Group ባለፈው ረቡዕ በጉዳዩ በወቅታዊ ይዞታ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን የሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ ተከታትለናል።

XS
SM
MD
LG