በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያው ተደጋጋሚ ድርቅ የአየር ንብረት ለውጡ ማሳያ ነው


የኢትዮጵያው ተደጋጋሚ ድርቅ የአየር ንብረት ለውጡ ማሳያ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:12 0:00

የኢትዮጵያው ተደጋጋሚ ድርቅ የአየር ንብረት ለውጡ ማሳያ ነው

ድርቅ ለአፍሪካ ቀንድ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ባለሙያዎች እንደሚሉት ግን በአየር ንብረት ለውጡ ሳቢያ በኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማልያ ሰብሎችና ከብቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እየገደለ ሲሆን ድርቁ ተደጋግሞ የሚከሰትበት መንገድ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ድርጅት፣ በድርቁ የተጠቁትን መመገብ ብቻ ሳይሆን፣ ድርቁን ለዘለቄታው መቋቋም የሚችሉ ማኅበረሰቦችን በመርዳት እየሰራ ነው፡፡

ሀዋ አብዲ ዎሌ በብዙ የድርቅ ክስተቶች ውስጥ ያለፉ በ70ዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሴት ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ እስከዛሬ ድረስ አራት የዝናብ ጊዜዎች በተከታታይ ሳይመጡ የቀረቡትን ጊዜ አያስታውሱም፡፡

ዋሌ ይህንኑ ሲገልጹ “ትልቅ ልዩነት እያየን ነው፡፡ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት ሰዎች ብዙ ዝናብ ይመለከቱ፣ እንስሳትም ብዙ ወተት ይሰጡ ነበር፡፡ በጣም ትልቅ ልዩነት አለው፡፡” ብለዋል፡፡

የዓለም ምግብ ድርጅት የሳቸውን መንደር እየረዳ ያለው ድርቁ ያስከተለውን ቀውስ እንዲቋቁሙ ብቻ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ ራሳቸውን መልሰው እንዲገነቡም ጭምር ነው፡፡

ዝናቡ መልሶ በሚዘንብበት ወቅት በደረቁ መሬት ላይ የሚፈሰውን ውሃ ለማቆር በግማሽ ክብ የሆነውን የአንድ ሜትር ስፋት ያለውን የውሃ ጉድጓድ እየቆፈሩ ነው፡፡

ስለዚህ ያኔ ሣሩም የበለጠ ሰለሚያድግ የህልውናቸው መሠረት የሆኑትን ከብቶችንም ይመግባሉ፡፡

ስለ ወደፊቱ መፍትሄ ሊሰጥ የሚችል እርዳታ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ሳይንቲስቶች የአየር ንብረት ለውጡ የዚህ ተደጋጋሚና አደገኛ ሁኔታ ዋነኛው ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ፡፡

በኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የሜትሮሎጂ አገልግሎት ድርጅት አቡባካር ሳሊህ ባቢከር እንዲህ ይላሉ

“በዚህ ቀጠና ያለው የአየር ንብረት ሁኔታ በአቅራቢያው ባሉ ውቅያኖስች የሚከሰተው ነገር ነጸብራቅ ነው፡፡ ይህ ሀሩር በሆነው አካባቢ ባለው ሞቃታማው የውቅያኖስ ክፍል በፍጥነት እየተስፋፋ የሚገኝ ሙቀት መሆኑን የሚያሳዩ ጥናቶች አሉ፡፡ ስለዚህ ሙቀቱ ባለፉት100 ዓመታት ውስጥ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው፡፡ ስለሆነም ይህ ሙቀት ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ከመጋቢት እስከ ሰኔ ካለው ወቅት ድርቀት ጋር የተገናኘ ነው፡፡”

ዝናቡ በሚመለስበትም ወቅት ከፍተኛ ጎርፍ ያስከትላል፡፡ እነዚህ ክስተቶች የአየር ንብረት ለውጡ ምሳሌዎች ብቻ አይደሉም እኩልነት ያለመኖሩንም ማሳያ ናቸው፡፡

በአዲስ አበባ የአየር ንብረት ለውጥ ፖሊሲ ባለሙያ ሀብታሙ አዳም እንዲህ ይላሉ

“ለአየር ንብረት ለውጡ፣ የኛን አስተጽኦ ከልቀቱ መጠን ጋር ስታስተያየው በጣም ጨርሶ የሚወዳደር አይደለም ምክንያቱም አብዛኛው ልቀት የሚመጣው ከበለጸጉት አገሮች ነው፡፡”

እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ አገሮች ውጤቱን የሚያስከትለውን አደጋ ለመቋቋም የገንዘብ ድጋፍ የላቸውም፡፡

የዓለም ሜትሮሎጂ አገልግሎት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጡን ለመቋቋም ከሰሃራ በታች ያሉ የፍሪካ አገሮች በዓመት እስከ 50 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋቸዋል፡፡

ያ እስተሟላ ድረስ የሚፈናቀሉና እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር መጨመሩ ይቀጥላል፡፡

በሶማሌ ክልል የዓለም ምግብ ድርጅት ተወካይ አሊ ሁሴን ስለዚሁ ሲናገሩ

“ይህን አስደጋጭ ነገር የሚመክት ማህበረሰብ መገንባት ያስፈልገናል፡፡ ያንን ለማድረግ እንደ ግማሽ ጨረቃ በመሳሰሉት፣ በረሃማ አካባቢዎችን መልሶ በማልማት፣ ለወደፊቱ ለማህበረሰቡም ሆነ ለከብቶች ይበልጥ ጠቃሚ እንዲሆኑ፣ የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴዎችን መልሶ አጽንኦት በመስጠት ማስተዋወቅ እንፈልጋለን፡፡” ብለዋል፡፡

በሶማሌ ክልል የሚካሄዱ እነዚህ ፕሮጀክቶች ስኬት እያሳዩ ሲሆን ሌሎችንም ብዙ ሰዎችንም ለመርዳት እንደ ሞዴል ተወስደው ሊደገሙ የሚችሉ ናቸው፡፡

በአካባቢው የመንደሩ ሽማግሌ የሆኑት ኢብራሂም ኩራባድ ፋራህ የዝናብና ወራጁን ውሃ በመጥለፍ መሬታቸው ላይ እየተሠራ ባለው መስኖ ተመልሶ የለማውን መሬታቸውን እያረሱ ነው፡፡

ፋራህ “እጅግ በርካታ ጥቅሞች ማግኘታቸውን ነው የተናገሩት፡፡ አሁን ማረስና ሳሩንም ለከብቶቻቸውና ለጎጆቻዎቻቸው ክዳን መጠቀም ችለዋል፡፡ እንዲሁም ውሃዉንም ለራሳቸውና በተለይም ከብቶቻቸውን ለማጠጣት እንደሚጠቀሙበት” ተናግረዋል፡፡

ከባቢውን አየር ተስማሚ ማድረጉ ለማህበረሰቡ ወሳኝ ቢሆንም የአየር ንብረት ለውጥ ሳይንቲስቶች ልቀትን መቀነስ ወደፊት እጅግ ሊከፋ የሚችለውን አደጋ በማስወገድ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ሆኖ እደሚቆይ ያስጠነቅቃሉ፡፡

XS
SM
MD
LG