በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራ ስደተኞች አቤቱታ


የኤርትራውያን ሰልፍ አዲስ አበባ
የኤርትራውያን ሰልፍ አዲስ አበባ

ትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ያሉ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ መሆኑን በመግለጽ መፍትሄ እንዲሰጣቸው የሚጠይቅ ሰልፍ ያካሄዱት በአዲስ አበባ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምላሽ እየጠበቁ መሆኑን ገለጹ።

ስደተኞቹ ትናንትና ባደረጉት ሰልፍ ትግራይ ክልል በሜገኙ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ጥቃት እየደረሰባቸው ስለሆነም ወደሌላ ቦታ ይዛወሩ ሲሉም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር ኤጀንሲ በበኩሉ ለስደተኞች የደኅንነት ከለላ እየሰጠን ነው ሲል ገልጿል።

ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮምሽን ማብራሪያ ለመጠየቅ ያደረግነው ጥረት ግን ለዛሬ አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኤርትራ ስደተኞች አቤቱታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:04 0:00


XS
SM
MD
LG