በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ: የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር “ለትውልድ የዘለቀ ጠብን አትርፏል” ሲሉ ከሠሡ


32ኛ ዓመት “የነፃነት በዓል” አከባበር ፟ አስመራ
32ኛ ዓመት “የነፃነት በዓል” አከባበር ፟ አስመራ

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈ ወርቂ፣ “የዋሽንግተን ዲሲ ቡድን” ሲሉ በጠሩት አካል ላይ ክሥ አሰሙ። ፕሬዚዳንቱ ወቀሳውን ያሰሙት፣ ዛሬ በተከበረው 32ኛ ዓመት “የነፃነት በዓል” ላይ ነው።

ዛሬ ረቡዕ፣ ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በአሥመራ ስታድየም በተካሔደውና በቀጥታ የቴሌቭዥን ሥርጭት በተላለፈው ዓመታዊ የ“ነፃነት በዓል” ላይ፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያይስ አፈ ወርቂ ባሰሙት ንግግር፣ “የዘንድሮው የኤርትራ የነፃነት በዓል፥ ለነፃነት የተካሔደው ትግል እና የተገኘው ድል፣ እንዲሁም የኋለኛው ተጋድሎ ውጤት ደምቆ በታየበት ወቅት የሚዘከር ነው፤” ብለዋል።

የዘንድሮው የኤርትራ የነፃነት በዓል፥ ለነፃነት የተካሔደው ትግል እና የተገኘው ድል፣ እንዲሁም የኋለኛው ተጋድሎ ውጤት ደምቆ በታየበት ወቅት የሚዘከር ነው፤”

ፕሬዚዳንቱ፣ የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር፣ በኤርትራ እና በሌሎች ሀገራት ላይ ያካሒደዋል ያሉት ፖሊሲ፣ “ለትውልድ የዘለቀ ጠበኛነትን አትርፏል፤” ሲሉ ከሠዋል፡፡ “የዋሽንግተን ቡድን” ሲሉ የጠሯቸውን ወገኖችንም፣ አገራቸው፣ “ከኢትዮጵያ ጋራ ጥላቻ ውስጥ እንድትገባ ሠርተዋል፤” ሲሉ ወንጅለው፣ “ወደፊትም ይቀጥላሉ” ሲሉ ስጋታቸውን አመልክተዋል፡፡ እነርሱን ለመመከትም፣ “ዐዲስ የትግል ዘይቤ ይጠይቃል፤” ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በዋናነት፣ “የዋሽንግተን ቡድን” በማለት በጠሩት የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ላይ በአነጣጠረው ንግግራቸው፣ የአሜሪካ ፖሊሲ ምንጊዜም ሌሎችን ለመጫን እንደሚሞክር ገልጸዋል፡፡ አሁን ግን፣ ሩስያ እና ቻይና፣ በዓለም መድረክ ላይ ባላቸው የወሳኝነት ሥፍራ፣ የኃይል ሚዛኑ እየተቀያየረ ነው፤ የሚል አቋም አንጸባርቀዋል።

ቀጣናዊ ጉዳዮችን በሚመለከት፣ ኤርትራ፥ አንድነት የሚያስቀድም መንገድ ይዛ እንደምትቀጥልና በአገራዊ ጉዳዮችም፣ ሕዝባዊ ዘመቻዎች እና ተነሣሽነቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። ዘመቻው፣ በየትኞቹ ዘርፎች እንደሚካሔድ ግን፣ ፕሬዚዳንቱ በዝርዝር ያወሱት ነገር የለም።

XS
SM
MD
LG