አዲስ አበባ —
የህወሓት ተዋጊዎች ገብተውባቸው በነበሩ የደቡብ ወሎ አካባቢዎች የጤና ተቋማት ላይ “ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል” ሲል የዞኑ ጤና መምሪያ ገልጿል።
ለዚህ ክስ እስካሁን ከህወሓት የተሰማ ምላሽ ባይኖርም ቀደም ሲል መሪዎቹ ይሰጧቸው በነበሩ መግለጫዎ ግን ታጣቂዎቻቸው በሲቪል ተቋማት ላይ ጉዳት እንደማያደርሱ ሲናገሩ ቆይተዋል።
የጤና ተቋማቱ አሁን የሚገኙበት ሁኔታ ቀድሞ ሲሰጡ የነበሩ አገልግሎቶችን ለማስቀጠል የሚያስችል አለመሆኑን የዞኑ ባለሥልጣናት አመልክተዋል።