በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታሊባን በሴቶች ላይ ተጨማሪ ገደቦችን አዘዘ


ፎቶ ፋይል፦ ሂጃብ/የፌት መሸፈኛ/ የለበሱ ሴቶች በካቡል ገበያ
ፎቶ ፋይል፦ ሂጃብ/የፌት መሸፈኛ/ የለበሱ ሴቶች በካቡል ገበያ

አፍጋኒስታንን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ታሊባን፣ ትናንት እሁድ በሴቶች ላይ ያወጣው አዲስ የጉዞ ህግ፣ "አሸባሪው ቡድን በሴቶች ላይ የሚደርገው ሌላ ተጨማሪ የበደል ድርጊት ነው" ስትል ዩናይትድ ስቴትስ ትችቷን አሰምታለች፡፡

በአፍጋኒስታን የበጎነት አስተዋዋቂና የክፋት መከላከል ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ፣ ሴቶች ከሌላ ሰው ጋር ካልሆኑ በቀር ብቻቸውን ከ72 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀው እንዳይጓዙ አዟል፡፡

የታክሲ አገልግሎት ሰጭዎችም የእስላሚክ ሂጃብ ወይም ራሳቸውን ለሸፈኑ ሴቶች ብቻ እንዲሰጡ መመሪያ ማስተላለፉ ተገልጿል፡፡

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ሳዲቅ አኪፍ ማህጀር ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ “ውሳኔዎቹ ከሸሪያና እስልምና ህግ ጋር አብረው የሚሄዱ ናቸው” በማለት የውሳኔውን አግባብነት ተናግረዋል፡፡

መመሪያው ወንዶች ብቻ በሚሰማሩበት የትራንስፖርት ዘርፍ ያሉ ወንድ አሸክርካሪዎች፣ ጺማቸውን እንዲያሳድጉ፣ ለጸሎት እረፍት እንዲወስዱና በመኪናዎቻቸው ውስጥ ሙዚቃ እንዳያጫዉት ያዛል፡፡

ይህ አስገዳጅ መመሪያ ከመውጣቱ ሳምንታት በፊት፣ በወጣ ሌላ መመሪያም፣ የአፍጋን ቴሊቭዥን ጣቢያዎች፣ የድራማና ተከታታይ አዝናኝ ፊልሞች ላይ የሚጫወቱ የሴት ተዋናዮችን እንዳያሳዩ አዟል፡፡

ዜና አንባቢ ሴቶች በሚያነቡበት ሰዐት ሂጃብ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ መተላለፉም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG