በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታጣቂዎች በአፍጋኒስታን የጦር ሆስፒታል ላይ ጥቃት አደረሱ


አጥፍቶ ጠፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ ታጣቂዎች ያሉበት ቡድን፣ ካቡል በሚገኘው በአፍጋኒስታን ትልቁ የጦር ሆስፒታል ላይ፣ ዛሬ ማክሰኞ ባደረሰው ጥቃት በትንሹ 15 ሰዎችን የተገደሉ ሲሆን ሌሎች በርካቶች ቆስለዋል፡፡

ስማቸውን ያልገለጹ አንድ ባለሥልጣን ጥቃቱ መድረሱን ያረጋገጡ ሲሆን የአፍጋኒስታን ዜና አገልግሎት የአይን እማኞችን ጠቅሶ ጥቃቱ የተፈጸመው “ዳኤሽ” ተብሎ በአገሬው ሰዎች በሚጠራው የእስላማዊ መንግሥት መሆኑን ዘግቧል፡፡

የአፍጋኒስታን መንግሥት ቃል አቀባይም ሁለት ቦምቦች ከሆስፒሉ መግቢያና ሆስፒታሉ ውስጥ መፈንዳታቸውን ገልጸዋል፡፡

ታሊባን ጥቃቱን ከፈጸሙ ሌሎች ታጣቂዎች ጋር ሆስፒታል ውስት የተዋጋ ሲሆን፣ በጥቃቱ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ በትክክል አልተገለጸም፡፡

XS
SM
MD
LG