በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፄ ምኒልክ በአድዋ ጦርነት የተዋጉበት ጎራዴ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ


አፄ ምኒልክ በአድዋ ጦርነት የተዋጉበት ጎራዴ/ኢዜአ/
አፄ ምኒልክ በአድዋ ጦርነት የተዋጉበት ጎራዴ/ኢዜአ/

አጼ ምኒልክ በአድዋ ጦርነት ላይ የተዋጉበት ጎራዴ ከዩናይትድ ስቴትስ ወደ ኢትዮጵያ መመለሱን ተገለጠ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዛሬ ባወጣው ዘገባ በወቅቱ ከጎራዴው ጋር ተዘርፎ የነበረው መስቀል ጨምሮ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ የተላላኳቸው ደብዳቤዎች፣ ፎቶግራፎች፣ ፖስት ካርዶችና የፁሁፍ እና የምስል ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴ ቅርሶቹን ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ያስረከበ መሆኑም በዘገባው ተመልክቷል፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አባባው አያሌው ወደ አገር የተመለሱትን ቅርሶች ጠብቆ የማቆየት ኃላፊነትን ተቀብለናል ያሉ ሲሆን በርክክብ ሥነ ስርዓቱ ላይ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴን ጨምሮ የማኅበሩ አባላትና እንግዶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG