የዘመናዊነት አንዱ ገጽታ የኾነው ከተማ እና ከተሜነት ሲስፋፋ፣ ኑሮን ለማሸነፍ እናትም አባትም ከቤት ውጭ ሥራ መሥራት ሲኖርባቸው፤ ሕፃናት ልጆች ገና በለጋ ዕድሜያቸው፣ በቴሌቪዥንና በእጅ ስልኮች ላይ በቀላሉ ለሚታዩ ምስሎች እና መተግበሪያዎች ተጋልጠዋል።
ኾኖም፣ ያልተገደበ የስክሪን ሰዓት አጠቃቀም፥ ለዐይን ሕመም፣ ለእንቅልፍ ዕጦት፣ ለትኩረት ማነስ፣ ለጠባይዕ ለውጥ እና አልፎ ተርፎም ለተለያዩ የአእምሮ ሕመሞች እንደሚያጋልጥ፣ የሕፃናት እድገት ባለሞያዎች ይናገራሉ።
ነዋሪነታቸውን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረጉት የቴክኖሎጂ ባለሞያዋ ወሮ. ነጻነት ቦጋለ፣ ወላጆች በተለይ በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ላይ በሚያጋሯቸው የልጆቻቸው ምስሎች እና ስኬቶች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ይመክራሉ።
ወሮ. ነጻነት፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ አድርገዋል፤ ቃለ ምልልሱን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም